Our Projects

Active Initiative

ለተቋሙ ሴት አሰልጣኞችና ባለሙያዎች የአመራርነት ስልጠና ተሰጠ።

የካቲት 22/2016 ዓ ም
በስልጠናው መጀመሪያ ላይ የተገኙት የEASTRIP ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ እንደተናገሩት የተቋሙን ሴቶች ለአመራርነት ብቁ ለማድረግ ታስቦ የሚሰጥ ስልጠና በመሆኑ በቀጣይ አራት ቀናት በተለያዩ ዕርሶችና በተለያዩ አሰልጣኞች የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ሴት ባለሙያዎችን ብቻ ያሳተፈው ስልጠና በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነና ቀጣይነት እንደሚኖረውም አቶ አብርሃም ጠቁመዋል።
የዛሬውን ስልጠና የሰጡት ከሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ አሰልጣኝ ወ/ሮ ኤደን ቡሽራ ሲሆኑ ስለ አመራርነት ምንነትና ሴቶች እንዴት ወደ አመራርነት መምጣት የሚችሉባቸውን መንገዶች አብራርተዋል።
ትክክለኛ የኢንስቲትቱን መረጃዎችን ለማግኘት የኢንስቲትዩቱን
ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/tticommunication ወይም
ቴልግራም https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት https://www.tti.edu.et/ ይጎብኙ
ለተቋሙ ሴት አሰልጣኞችና ባለሙያዎች የአመራርነት ስልጠና ተሰጠ።
Active Initiative

ፕሮጀክቱ ከሰራተኞች አቅም ማጎልበቻ ባሻገር ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ የሚገኘውን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

EASTRIP ፕሮጀክት ከሰራተኞች አቅም ግንባታ ባሻገር ለኢንስቲትዩቱ የተሰጡ ተልዕኮዎችን እንዲሁም ከትላንት ጀምሮ በተሰጠው ስልጠና ወቅት የተለዩ ችግሮችን በመፍታት ተልዕኮውን እንዲወጣ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሀም ለገሰ ገለጹ።
ከታህሳስ 26 ጀምሮ እየተሰጠ ነበረው የችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ ስልጠናው በተቋም ደረጃ የሚታዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለመተንተና ችግሮችን ለመለየት የሚያግዝ እንደሆነ የገለጹት አቶ አብርሃም ለገሰ ተመሳሳይ አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቀጣይነት ይሰጣሉ ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ ፕሮጀክቱ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ፣ የኢንዱስትሪውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናት ላይ የተመሰረቱ የስልጠና ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ ማድረጉን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራ፣ ስልጠናዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ በአጠቃላይ ኢንስቲትዩቱን ወደ ልህቀት ማዕከል ሊያሻግሩ የሚያስችል ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ አብራርተዋል ።
ስልጠናው ላይ ከተሳተፉት መካከል የቮኬሽናል ጋይዳንስና ትብብር ስልጠና አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ በበኩላቸው የተሰጠው ስልጠና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር እየሰራና የሪፎርም ስራዎች እየተካሄዱ ባለበት በመሆኑ ወቅታዊ እንደሆነ ገልጸዋል።
በማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ውስጥ የታቀዱ ስራዎች ሁሉንም በሚያሳትፍ መልኩ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰራተኞች በቀላሉ ለማሳተፍ ያግዛል ያሉት አቶ ታደሰ ሞላ የተቋሙ እቅዶችን ለማሳካት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በስልጠናው ላይ በግብዓት፣ በቅንጅታዊ አሰራር፣ እቅድን መሰረት አድርጎ ከመስራትና ሌሎችም ኢንስቲትዩቱ ተልዕኮውን በአግባቡ እኔዳይወጣ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሰራተኞችም በቀጣይነት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
ፕሮጀክቱ ከሰራተኞች አቅም ማጎልበቻ ባሻገር ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ የሚገኘውን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
Active Initiative

ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ግንባታን አስመልክቶ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ

ቱ.ማ.ኢ የካቲት 08/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በEASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት የልህቀት ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ በሚገኘው ግንባታ ዙሪያ ከወረዳው ነዋሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ አንድ ፕሮጀክት ሲገነባ ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ የስልጠና፣ የሥራ ዕድል እና ሌሎች የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ይዞ እንደሚመጣ ገልጸው፤ ማሰልጠኛው የሚገነባው የቱሪዝም የልህቀት ማዕከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪም በዚህ ተጠቃሚ ስለሚሆን ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩሉን ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግ በመልእክታቸው ገልጸዋል።

የተቋሙ EASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ እንደገለጹት ይህ ፕሮጀክት ወደ አካባቢ በመሄዱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የማይጠቀም የማህበረሰብ ክፍል እንደማይኖር ገልጸው። ይህም ተቋሙ በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ በመደበኛ በቀንና በማታ በቅዳሜና እሁድ በአጫጭር እና ረዥም ስልጠናዎችንና ምርምርና ማማከር እንዲሁም በርካታ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን የሚሰጥ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች ወ/ሮ ሳይደያ ከይረዲን እንደተናገሩት ይህ ትልቅ ተቋም ወደ ወረዳችን መምጣቱ ትልቅ እድል ነው በማለት ተቋሙ ሀገር አቀፍ በመሆኑ ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር እንድንጠቀም ይረዳናል ብለዋል።
አቶ ፍቅሩ ዳኛው እና አቶ አብርሃም ዲቢንቶ ሌሎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፕሮጀክቱ ወደ አከባቢያችን መምጣቱን እንደ ትልቅ ጸጋ እናየዋለን በማለት ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠበቀውን ሁሉ አብሮ ለመስራትና ወክለው የመጡትን ነዋሪ ስለተቋሙ ለማሳወቅ ፍቃደኞች መሆናቸውን ገልጸዋል የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱንም ጎብኝተዋል።
የግንባታ ቦታው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 12 መሆኑ ከዚሀ ቀደም መጥቀሳችን ይታወቃል ።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ግንባታን አስመልክቶ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ
Active Initiative

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ቱ.ማ.ኢ የካቲት 08/2017 ዓ.ምበአዲስ አበባ ከተለያዩ ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ አካል ጉዳተኛ ህጻናት ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የትምህርት ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ተቋሙ በአካባቢውና አጎራባች ክፍለ ከተሞችም የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ተግባራትም እንደሚሳተፍ ይታወቃል።ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.e
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።
Active Initiative

የዓለም ባንክ ግዥ ሥርዓት እና ኤሌትሮኒክስ ግዥን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።

ቱ ማ ኢ ጥር 15/2018 ዓ ምበቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከዓለም ባንክ ድጋፍ EASTIRP ፕሮጀክት ግዥ ሥርዓቱ ወደ ኤሌክትሮኒክስ በመቀየሩ ሥራው ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።ስልጠናውን የከፈቱት የተቋሙ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የነበረውን የግዥ ሥራ ጫና የሚቀንስና የጊዜና ጉልበት ቆጣቢ የሆነውን ሲስተም ሥራው የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና የEASTIRP ፕሮጀክት ባለሙያዎች ይህንን ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመውሰድ የግዢ ሥራው ቀልጣፋ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

በመቀጠልም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ሁሉም በትኩረት በመከታተል የተገኘውን እድል መጠቀም መቻል እንዳለበት አሳስበዋል።
ስልጠናው የሚያካትተው ስለ EGP ምንነት፣ ጠቀሜታው እና ቀጣይ አሰራሮችን እንደሆነ የጠቆሙት ከፌዴራል ግዥና ፋይናንስ ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ ዋለልኝ አሰፋ እና አቶ ሀብተወልድ ተሾመ ናቸው።
አራቱን የግዥ አይነቶች አቅርቦት፣ ግንባታ ፣ አገልግሎት እና ማማከር ወረቀት አልባ በሆነ መንገድ እንዴት መስራት እንደሚቻል ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በተቋማችን ላለፉት ሦስት ዓመታት በወርልድ ድጋፍ የEASTIRP ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።
​ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et
የዓለም ባንክ ግዥ ሥርዓት እና ኤሌትሮኒክስ ግዥን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
Active Initiative

የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን አባላት ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።

ቱ ማ ኢ ህዳር 27/2018 ዓ.ም ከታንዛኒያ INSTITUTE OF ACCOUNTANCY ARUSHA ተቋም የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ። የልዑካን ቡድኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተቀብለው በጋራ ተወያይተዋል።
አቶ ጌታቸው በውይይቱ እንደገለጹት ከታንዛንያ የቱሪዝም ኮሌጅ ጋር በስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ የመግባቢያ ስምምነት አድርጎ አብረው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው ለአሩሻው አካውንታንሲ ኢንስቲትዩት ልኡካን ቡድን ስለተቋሙ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ገለፃ አድርገዋል።
የልኡካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱን የሥራ ክፍሎች እና አንጋፋውን የገነት ሆቴል ቦሊንግ መጫወቻ ጎብኝተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/
የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን አባላት ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ።