20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እና ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እና ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ
ቱማኢ
ህዳር 30/2018 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሄራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል፤ 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን "ትውልድን በስነምግባር ፣ ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ።
በዓሉን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ባስተላለፉት መልዕክት እኛ ኢትዮጵያዊያን ባለብዙ ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ እና በሀይማኖት የደመቅን በልዩነታችን ውስጥ ውበታችን የደመቀ ህዝቦች ነን ካሉ በኋላ በዓሉ በፌዴራል ተቋማት ደረጃ እንዲከበር የተፈለገው፣ ህብረብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ እና የህገ መንግስት አስተምህሮ ሥራዎች እንዲጎለብቱ ለማድረግ እስከሆነ ድረስ ሁላችንም የሚጠበቅብንን አስተዋጽዖ ማበርከት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ እንደገለጹት ሙስና ሀገርና ትውልድን የሚያቀጭጭ የብልጽግና እንቅፋት በመሆኑ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መከላከል የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን በውል ተገንዝበን፣ የጀመርነውን ተቋማዊ ለውጥ በላቀ ደረጃ በማጠናከር.፣ የአገራዊው የፀረ-ሙስና ትግል አካል ሆነን ትውልድን በማነጽ ረገድ የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዕለቱን አስመልክቶ የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀው በድምፅ የተቀረፀ መልዕክት ለሠራተኛው ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/